The Kefita team at the groundbreaking ceremony, January 2021

February 12, 2021

The KEFITA Groundbreaking ceremony took place on Thursday 21st January 2021 at the location of KEFITA|ከፍታ a G+20 exclusive gated apartment building to be completed by the Middle of 2025, off Embassy Row in the Signal district of Addis Abeba.

‘ከፍታ’ የሚለው የአማርኛ ቃል ግዝፈትን እና ልህቀትን እንደማመልከቱ የሮክሶቶንን ራዕይ ጠቅለል አድርጎ ይገልጻል።

በኢትዮጵያ የሮክስቶን ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ዲየትሪች ሮጊ እና የሮክስቶን ኢትዮጵያ ኃላፊ ሚስተር ቤንጃም ቬተርሊ የግንባታውን ስራ ለሁዋሆንግ ኮንስትራክሽን አስረክበዋል። እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን በደስታ እያበሰርን እ ኤ አ በ ፌብሩዋሪ 2021 ስራዎች ሙሉ ለሙሉ እንደሚጀመሩ ልንገልጽ እንወዳለን።

ይህንጻው ንድፍ የኢትዮጵያን ቅርስና ባህል ከግምት ያስገባ ሲሆን ከፊት ለፊቱ የሚኖረው መልክ የአገር ውስጥ የጨርቅ ላይ ንድፎችን መነሻ በማድረግ የሚሰራ እንዲሁም እያንዳንዱ የከፍታ ሃሳብ እና አሰራር የሚወክላቸውን ነገሮች ከሚቆምላቸው ጽንሰ ሃሳቦች ጋር አጣምሮ የያዘ ነው። ከፍታ ዓለም አቀፍ የንድፍ እና የግምባታ ድረጃዎችን ጠብቆ ጥራት ያላቸው አገልግሎት መስጫዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በጥንቃቄ በባለሞያዎች ቁጥጥር የሚከናወን ነው። በኢትዮጵያም የአረንጓዴ ህንጻ እውቅና ወይም ኢዲጂኢ የሚባለውን የምስክር ወረቀት ማግኘት የቻለ የመጀመሪያው የመኖሪያ ህንጻ ነው።

Guests and contractors arrive to the Kefita groundbreaking ceremony

በብሩህ ሰማይ ስር ቀይ ምንጣፍ ተዘርግቶ እንግዶቻችን እንደ አመጣጣቸው በከፍታ ላይ ዳናቸውን እያሳረፉ እንዲራመዱ ተደረገ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜን ጨምሮ መስራች የቡድን አባላት (አፓርትመንት ሊገዙን ቃል የገቡልን የኢትዮጵያ የንግድ ባለሞያዎች) እንዲሁም የ ሴበረስ ፍሮንቲየር ማርኬጽ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ግሬግ ሜትሮ በክብር እንግድነት ተገኝተውልንም ነበር።

Commissioner Lelise Neme, Ethiopian Investment Commission (EIC)

ባለድርሻ አካላትን፣ የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን እና ጋዜጦችን እንዲሁም በግንባታው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙትን ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ተቀበልን። በ ዲየትረች ሮጌ ለእንግዶች ስለከፍታ የመግቢያ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ሮክስቶን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ዕቅድም ተጠቅሷል።

Dietrich Rogge, CEO ROCKSTONE
Speeches from the Kefita groundbreaking ceremony

የፊርማ ማኖር ስርዓቱ በቦታው የተገኙትን ሁሉ በፈገግታ የሞላ ደማቅ ክስተት ነበር። ቡድኑም ይህን ፈር ቀዳጅ እንቅስቃሴ ለማስጀመር ባለደርሻ አካላትን በሙሉ አካቶ የግንባታ ማስጀመሪያውን አካሂዷል።

Signing of the Kefita construction contract with HuaHong

ይህ አዝናኝ ሆኖ በወሳኝ እንቅስቃሴዎች የተሞላው ስነ ስርዓት ከመጠናቀቁ በፊት እንግዶችን ለምግብና መጠጥ በመጋበዝ፣ የግንባታ ስፍራውን ዞር ዞር ብለው እንዲያዩት በማድረግ እንዲሁም የከፍታ ቤተሰብ በጋራ ዘና እንዲል በመጋበዝ ተጠናቋል።

Kefita groundbreaking ceremony

በመጨረሻም ቀኑን አስውባ የቆየችው ጀምበር መጥለቂያዋ ተቃረበ ዝግጅቱንም የታደመ ሁሉ የመዝናናት ስሜት ውስጥ ሆኖ ባለ 21 ፎቁን የከፍታ አፓርትመንት በአዲስ አበባ አድማስ ላይ ለማየት የሚያስችል የመንፈስ ከፍታን ታጥቆ ማስጀመሪያውን ተሰናበተ።

Sundown on Kefita