የከፍታ ወለል
በከፍታ ህንጻዎች አንድ ሙሉ ወለል ለነዋሪዎች እና ለእንግዶቻቸው ከተሟላ የመዝናኛ አቅርቦት ጋር ለማረፊያነት የተመደበ ነው። ይህ የከፍታ ወለል በአይነቱ ልዩና ምቹ የሆነ የስራ፣ የመሰብሰቢያ እንዲሁም ከወዳጅ ዘመዶች ጋር ዘና የሚሉበት ስፍራ ነው። የከፍታን ወለል ንድፍ ያዘጋጀው ቡድናችን የደንበኞቻችንን ፍላጎቶች በጥልቀት በመመርመር ለነዋሪዎቻችን የሚስማማውንም በመምረጥ ነው።
የከፍታ ወለል ሰዎች ቡና ወይም የተለያዩ መጠጦችን ይዘው በግል የሚዝናኑባቸው ቦታዎችን ያካትታሉ። ለመዝናናትና ጥብስ ለመጥበስ /ባርባኪዩ/ የሚመች የአዲስ አበባን ውብ የአየር ንብረት እያጣጣሙ እስከ የካ ተራራ የሚዘረጋ እይታን የሚለግስ ከተማዋንም ወደታች የሚያስቃኝ ልዩ ሰገነት ያካተተ። ለክብረ በዓላትና ከወዳጅ ዘመድ ጋር ለሚከበሩ የተለያዩ ዝግጅቶች ከአገልግሎት ጋር የሚቀርብ 150 ሰዎች ገደማ ማስተናገድ የሚችል ቦታ ነው። የከፍታ ወለል በ 300 ሜትር ስኩየር ቦታ ላይ ያረፈ የአካል ብቃት ማዘውተሪያ /ጂም/ እና ስፓ ያለው እንዲሁም ለዮጋ መስሪያ የሚሆን ቦታንም ለወንድና ሴት በተናጥል የተዘጋጀ ሳውናን እንደ አስፈላጊነቱ ሊቀየር ከሚችል ቦታ ጋር የያዘ ነው። በተጨማሪም የተለያዩ የስብሰባ እና የጋራ መስርያ ስፍራዎች ፀጥታ አና ምቹ የስራ አካባቢዎች የያዘ ወለል ነው፡፡
ለዚህ ተብለው በተመደቡ ሶስት አሳንሰሮች ከመሬት ወለል የሚያገናኙት ሲሆን የከፍታ ወለልን ወደየ መኖሪያ አፓርትመንቶች እንዲሁም የመኪና ማቆሚያዎችም ያገናኛሉ።
የአቀባበልና መልዕክተኛ አገልግሎቶችም እንደ ነዋሪዎች ፍላጎት የሚያቀርብ ቦታ ነው።


እንግዳ መቀበያ እና የቡና ላውንጅ
150 እንግዶች የሚያስተናግድ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች
የጋራ የመስሪያ ቦታ
ከሰገነቱ ጋር የሚያያዙ የጂምናዝየም እና የዮጋ ክፍሎች
ለወንድና ሴት በተናጥል የተዘጋጀ ሳውና እና ልብስ መቀየሪያ ክፍሎች ከበረንዳ ጋር
የሰገነት መናፈሻ
ህንጻ ውስጥ የአትክልት ስፍራ
የልጆች ቦታዎች
ከመኪና ማቆሚያ እስከ እንግዳ መቀበያ የሚያደርሱ ሁለት አሳንሰሮች
እንግዳ ተቀባዮች
አስተማማኝ ጥበቃ እና ተቀባይ ያለው የሚኪና ማቆሚያ
የ24 ሰዓት የጥበቃ አገልግሎት



