ባለ ሁለት መኝታ +
አነኚህ ሁለት መኝታ + የመኖሪያ አፓርታማዎች ግዙፍና በርካታ ክፍሎችን ያካተቱ ናቸው፡፡ የክፍሎቹ ስፋት እጅግ ማራኪና ቀልብን የሚገዛ ሲሆን ምቹ እና የተንጣለለ ሳሎን ከመመገቢያ አዳራሽ ጋር፣ እንዲሁም አረፍ ብሎ ለመወያየት እና ለመመገብ ስፍራ ካለው የተሟላ ማዕድ ቤት (ኪችን) ጋር ያካተቱ ናቸው፡፡
መኖርያ አፓርታማዎቹ ትልቅ ዋና መኝታ ቤት እና ከመኝታ ቤቱ ጋር የተያያዘ ሰፊ ስፍራ ያለው መታጠቢያ ክፍል እንዲሁም ተጨማሪ መኝታ ክፍል ያካተቱ ናቸው፡፡ የተጨማሪ መኝታ ክፍሉ ንድፍ ከዋናው ክፍል ጋር ሳይገናኝ ለእንግዶች ማረፊያ እንዲያመች ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
ሁሉም አፓርታማዎች ላውንደሪ/የዕቃ ክፍል ያላቸው ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ አፓርታማዎች ደግሞ የረዳት ክፍሎች እና ቴራስ የተሟላላቸው ናቸው፡፡
ለጥንዶች እና ለትናንሽ ቤተሰቦች እንዲሁም ሰፋፊ መኖሪያዎችን ለሚፈልጉ ላጤዎች የተመረጡ ናቸው፡፡
ዋና መኝታቤት ከመታጠቢያ ቤት ጋር
እንደ አማራጭ የሚቀርብ ውስጡ ሰው የሚነቀሳቀስበት የልብስ ማስቀመጫ ክፍል
ዘመናዊ መታጠቢያ ቤት
- ሰፊና የተቀናጀ የመመገቢያና የመኖርያ እልፍኝ
- ከወለል እስከ ጣሪያ የሚደርሱ የእልፍኝ መስኮቶች
እንደ አማራጭ የቀርቡ የተለያዩ በረንዳዎች
እንደ አማራጭ የሚቀርብ ክፍት የምግብ ማዘጋጃ
የልብስ ማጠቢያ እና የዕቃ ማስቀመጫ ክፍል በአንድ ላይ
እንደ አማራጭ የሚቀርብ የቤት ውሰጥ ረዳት ክፍል
ሁለት የሰው አሳንሰር
ለእቃና ለሰው የሚሆን አሳንሰር
የተመደበ የመኪና ማቆሚያ
- ለእንግዶች የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት
- የከፍታ ወለልን መጠቀም
- የአቀባበልና መልዕክተኛ አገልግሎት
- የ24 ሰዓት የጥበቃ አገልግሎት
- *የአፓርትመንቶቹ ገፅታዎች በጊዜው ግኝት የሚወሰኑ ይሆናሉ




