አዲሰ የአፍሪካ አድማሰ

green down arrow

ከፍታ በአዲስ አበባ፣ ሲግናል አካባቢ ኤምባሲዎች በርከት ብለው ባሉበት ቦታ ይገኛል

ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ናት። የትም የማይገኝ ውበትን ከተፈጠሮ ሃብት ጋር የታደለች ምድር ናት።

ሰፋፊና ለእርሻ ምቹ የሆኑ ለም መሬቶች፣ የተዋቡ ጥቅጥቅ ደኖች፣ ታላላቅ ወንዞች እንዲሁም የዓለም ሞቃት ቦታ የሚባለውን ዳሎልን የያዘቸው ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንቅ ተዓምር ነች። በተጨማሪም ከአፍሪካ አንጋፋዋ ነጻ አገር ስትሆን በእርግጥ በአለምም ጥንታዊ ከሚባሉት ቀደምት ተርታ ነች። እንደ ስልጣኔ መነሻነቷ የዳበረ ባህል የሚጋሩና በታሪክ የተሳሰሩ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች መገኛ ናት።

ኢትዮጵያ አሁንም የማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ እንደመሆንዋ እና ወደ ብሩህ ተስፋ እያቀናች እንደመሆኑ ይህንን አጋጣሚ ከ 110 ሚልየን በላይ ከሆኑት ህዝቦችዋ ጋር ስንጋራ ኩራት ይሰማናል።

World map showing flight times from key cities to Addis Ababa

የ ‘ይቻላል’ ከተማ

አዲስ አበባ ከተመሰረተችበት ከ19ኛው ክፍለዘመን አንስቶ ወደ ላ ዓለም የምትወስድ ተዓምረኛ ከተማ ናት።

አፍሪካ ውስጥ መታየት አለባቸው ከሚባሉ ቦታዎች አንዷ አዲስ አበባ ናት። በፍጥነት በማደግና በመለወጥ ላይ ያለች ዓለም አቀፍ ንግዶችን፣ ስነ-ጥበብ እና ባህልን ያዋሃደች የብዙዎች መናገሻ ናት።

ከተማዋ ባላት ለንግድ ምቹ የሆነ ሁኔታ እና አቅም የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ታይቶ ለማይታወቀው አስደናቂ ዕድገት ቁልፍ ሆናለች።

አዲስ አበባ ለአህጉሩ ባላት የታሪክ፣ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ሚና የተነሳ የአፍሪካ መዲና በመባል የምትጠራ ሲሆን የአፊርካ አራተኛ ትልቋ ከተማ እና የዲፕሎማቲክ መዲና፣ 115 የዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች፣ 170 መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫም ነች።

Outline map of Ethiopia showing major towns and cities
Addis Ababa at night
Green fields in Ethiopia with mountain peaks rising behind
Addis Ababa airport

የኤምባሲዎቹ መናገሻ፣ ሲግናል

ባለሞያዎቻችን መሃል አዲስ አበባን በስፋትና በጥልቀት መርምረው ሲግናል አካባቢን ለከፍታ መገኛነት ሲመርጡ በታላቅ ደስታ ነበር። እንደ አንድ የከተማዋ ቀደምት ሰፈር ሲግናል ምቹና የጎለበተ መሃል አዲስ አበባ የሚገኝ ሚየመኖሪያ መንደር ሲሆን ከንግድ ተቋማት፣ ትምህርትቤቶች፣ የሆቴልና መሰል አገልግሎቶች እንዲሁም የዲፕሎማት መገኛዎች በሙሉ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቦታ ነው።

የከፍታ ህንጻ ከዋናው መንገድ በ30 ሜትር ርቀት ላይ ነጠል ብሎ በግርማ የተሰየመ ሲሆን ወደመግቢያው የሚያደርሰው መንገድም ግራ ቀኙን በዛፎች የተሰመረ ነው። ከፍታ በተጨናነቀ የከተማ ከባቢ ውስጥ ያለ ሰላማዊ የመኖሪያ ደሴት ነው።

የከፍታ ህንጻ ከዋናው መንገድ ወደ ላይ 30 ሜትር ለብቻው ዘለግ ብሎ የሚታይ ሲሆን ወደ መግቢያው የሚያደርሰውም መንገድ ግራና ቀኙ በዛፎች የተከበበ ነው። ከፍታ የተጨናነቀው ከተማ መሃል እንደ ደሴት ያለ ውብ ስፍራ ነው።

0 ደቂቃ
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ
0 ደቂቃ
ሒልተን ሆቴል
0 ደቂቃ
ሃያት ሪጀንሲ
0 ደቂቃ
ቅዱስ ገብርኤል ጠቅላላ ሆስፒታል
0 ደቂቃ
የብሪቲሽ፣ ቤልጂየም፣ ሩሲያ እና ኬኒያ ኤምባሲዎች
0 ደቂቃ
የጀርመን ፣ የጣሊያን እና የፈረንሳይ ኤምባሲዎች
0 ደቂቃ
የአሜሪካ ኤምባሲና የተባበሩት መንግስታት 20
0 ደቂቃ
ሳንፎርድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት (ብሪቲሽ) እና የጀርመን ትምህርት ቤት
0 ደቂቃ
ግሪክ ትምህርትቤት
0 ደቂቃ
ፍሬንች ትምህርት ቤት
0 ደቂቃ
የአሜሪካ ትምህርት ቤት
0 ደቂቃ
ሸዋ ሱፐርማርኬት

ኢትዮጵያ የሰው ዘር መነሻ ስትሆን የአህጉሩም ማዕከል ነች። ይህች ታላቅ የብዝኃነት ምድር፣ የታሪክ ሃብታም እና የበርካታ ዕድሎች ቋት የሆነች አገር እንግዳ አክባሪነትን ሰው ከመሆን ጸጋ ጋር ይዛ እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆን ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅምን የታደለች ነች። ከፍታ ደግሞ የኢትዮጵያን ትላንት፣ ዛሬ እና ነገን አጣምሮ ይዟል።

Kefita embodies Ethiopia’s past, present and future.

Play the Kefita video