ባለ አራት መኝታ
እነዚህ ልዩ ባለ አራት መኝታ አፓርታማዎች ከፍተኛ ምቾት እና ነፃነትን እንዲሰጥ በሚያስችል የተለየ ዲዛይን የተሰሩ የመኖርያ ስፍራዎች ናቸው፡፡ ማራኪ የሆነው የወለል ንድፍ ስራቸው ለቤተሰብ በቂ እና ምቹ የሆነ እጅግ ሰፊና ውብ ክፍል፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር አስደሳች ጊዜ ለማሳለፍ ወይንም ስራን ከቤት ሆኖ በምቾት ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡ የመኖርያ ቤት ዲዛይኑ አስደሳችና ቁልፍ ገፅታ ሠፊ ሳሎኑን ከመመገቢያ ክፍሉ እና ቅርፁን እንደፈለጉት አድርጎ ለመጠቀም ከሚመቸው ማዕድ ቤት (ኪችን) ጋር ያጣመረ መሆኑ ነው፡፡
መኝታ ቤቱ ሰፊ ክፍል አና ዋና መታጠቢያ ክፍል ያካተተ ነው፡፡ ሌሎቹ መኝታ ክፍሎች የጋራ መፀዳጃ ቤት እና ልዩ የእንግዳ መታጠቢያ ክፍል አላቸው፡፡ አራተኛው መኝታ ቤት እንደ መስሪያ ክፍል ሊያገለግል ይችላል፡፡ እነዚህ አፓርታማዎች ለቤተሰብ ምቹና አስደሳች ህይወት በቂ ክፍሎችን ያሟሉ ናቸው፡፡
- ዋና መኝታቤት ከመታጠቢያ ቤት ጋር እና ሰው የሚነቀሳቀስበት የልብስ ማስቀመጫ ክፍል
ትልቅ እና አነስተኛ መኝታ ክፍሎች
የእንግዳ መጸዳጃ ቤት
እንደ አማራጭ የሚቀርብ ክፍት የምግብ ማዘጋጃ
- ሰፊና የተቀናጀ የመመገቢያና የመኖርያ እልፍኝ
እንደ አማራጭ የቀርቡ የተለያዩ በረንዳዎች
- ከወለል እስከ ጣሪያ የሚደርሱ የእልፍኝ መስኮቶች
የልብስ ማጠቢያ እና የዕቃ ማስቀመጫ ክፍል በአንድ ላይ
ሁለት የሰው አሳንሰር
ለእቃና ለሰው የሚሆን አሳንሰር
የተመደበ የመኪና ማቆሚያ
- ለእንግዶች የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት
- የከፍታ ወለልን መጠቀም
- የአቀባበልና መልዕክተኛ አገልግሎት
- የ24 ሰዓት የጥበቃ አገልግሎት
- *የአፓርትመንቶቹ ገፅታዎች በጊዜው ግኝት የሚወሰኑ ይሆናሉ




