ህልምዎን እንገነባለን

green down arrow

ሮክስቶን

ሮክስቶን የተሟላ የሪል ስቴት ልማትና የኢንቨስትመንት አስተዳደር አገልግሎት የሚሰጥ በጀርመን፣ ስፔን እና ፖርቹጋል እንዲሁም በኢትዮጵያ ቢሮዎች ያሉት መቀመጫውን በጀርመን ያደረገ የግምባታ ተቋም ነው። በ 2018 እ.ኤ.አ በአፊሪካ የመጀምሪያው የሆነውን ቢሮውን ለመክፈት ኢትዮጵያን መርጧል።

ዋነኛ ትኩረቱም ጥራትን የጠበቁ ለመኖሪያና ለንግድ የሚሆኑ የሪል ስቴት ፕሮጀክቶችን ከ25 - 75 ሚልየን በሚደርስ ወጪ በዋና የቢዝነስ መገኛዎች እና መኖሪያ መንደሮች ሞያዊ አገልግሎቶችን እየሰጡ ዘመናዊ ንድፍን ከአስተማማኝ ግምባታ ጋር ማቀረብ ነው።

በአሁን ሰአት 650 ሚልየን ዶላር የሚያወጡ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ ሲሆን ሮክስቶን ሪል ስቴት ላይ ያለውን የካበተ ልምድ ከራሱ መነሻ ካፒታል እና ንቁ የሪል ስቴት አስተዳደር ጋር አጣምሮ ስራ ላይ ያውላል።

https://www.rockstonere.com/en/

The Kefita team

ቢጋር

ቢጋር አልሚዎች እና ገንቢዎች በ2012 እ.ኤ.አ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአራት አጋሮች የተቋቋመ ሲሆን በስነ-ህንጻ፣ ምህንድስና፣ የከተማ ልማት እና በፕሮጀክት አስተዳደር ከ40 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ አለው።

ባለሞያዎቹም ውጤታማ ንድፍን እና የግምባታ ሂደትን በግምባታ ዘርፉ ውስጥ ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ናቸው። ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠውም በጋራ መስራትን፣ ውይይትን፣ ውጤታማ ክርክርን እና ለውጥን ያለመ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በአንዳንድ ምሳሌዎች እንዳስመሰከረው የተገነባውንም አከባቢ ማስጠበቅ ላይ ነው። ቢጋር ከመነሻው ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመንግስትም ሆነ ለግሉ ዘርፍ እንዲሁም ለዲፕሎማቲክ ማሕበረሰቡ መጠነ ሰፊ የግምባታ ስራዎችን ለመስራት በኃላፊነት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ቢጋር ከ 5 - 50 ሚልየን ዶላር የወጣባቸው ፕሮጀክቶች ላይ በንድፍ ስራና ፕሮጀክት በማስተዳደር ተሳትፏል።

በተጨማሪም ቢጋር የመልሶ ማስዋቢያ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች የአገሪቷ መዳረሻዎች የሚገኙ ዝነኛ ህንጻዎችን እድሳት ክትትል አድርጓል።

Render of child's bedroom in Kefita, Addis Ababa

ሴርቤረስ

ይህ በኢትዮጵያ የሚገኘው ልማት በ2018 እ.ኤ.አ ሴርቤረስ ካፒታል ማኔጅመንት ከተሰኘው ድርጅት ጋር በሽርክና የተመሰረተ ነው።

በ 1992 እ.ኤ.አ የተመሰረተው ሴርቤረስ በተለያዩ ኢንቨስትመንት አማራጭ መስኮች በዓለም አቀፍ ደረጃ መሪ ሲሆን 42 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ንብረት በሪል እስቴት፣ ብድር እና የግል ንብረት አስተዳደሮች ውስጥ አሉት።

ሴርበኤረስ ፍሮንቲየር (በቀድሞ ስሙ ኤስ/ጂ/አይ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ኢክዊቲ ኢንቨስተር ሲሆን በአገሪዏ ውስጥም ከ11 ዓመታት የሚበልጥ ልምድ አካብቷል።

ሴርቤረስ ሪል እስቴት በዓለም ዙሪያ ከ575 በላይ በሆኑ ግብይቶች ወደ 29 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ከዓለማችን ግዙፍ የሪል እስቴት ኢንቨስተሮች ተርታ ተሰልፏል።

https://www.cerberus.com/

Exterior render of Kefita, Addis Ababa, looking down from above

ኡርኮ ሳንቼዝ አርክቴክቶች

በንድፍ ልህቀትና በአፍሪካ ምርጥ ስራዎቹን በማስመስከር ሽልማትና እውቅና ማግኘት የቻለ መቀመጫውን በኬንያ እና ስፔን ያደረገ በምስራቅ አፍሪካ፣ አውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የከወነ ተቋም ነው።

የኡርኮ ሳንቼዝ ባለሞያዎች ሃሳቦችን ለማንሸራሸር ዝግጁ የሆኑ፣ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡና በዓለም አቀፍ የምህንድስና መድረክ ላይ ያሉ ኮኮቦች ናቸው።

ኡርኮ ሳንቼዝ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት የካበተ ልምዱን ተጠቅሞ በአዳዲስ ፈጠራዎች የተሞሉና ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ምቹ የሆኑ ገጽታዎች ያላቸው የስነ-ህንጻ ንድፎችን ያበጃል። ፕሮጀክቶቹም በመጠን፣ በውስብስብነታቸው እና በሚሰጡት አገልግሎት አይነታቸው እጅግ የተለያዩ ናቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ተቋሙ በደንበኞች ዘንድ ታማኝነትን ማግኘትን እና ጽንሰ-ሃሳቦቹን አቻ በማይገኝለት መንገድ ወደ ተግባር እና አፈጻጸም መቀየርን በእሴትነት ይዞ ይንቀሳቀሳል።

Urko Sanchez, Architect of Kefita, Addis Abeba

አንጉሎራሶ

አማካሪ መኃንዲሶች

አንጉሎራሶ እኤአ በ 2002 እ.ኤ.አ የተመሰረተ በመላው አፍሪካ እና አውሮፓ በተቀናጁ ቢሮዎቹ በኩል ለግንባታው ኢንዱስትሪ የምህንድስና አገልግሎቶችን የሚሰጥ ተቋም ነው። ከ20 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ ባላቸው እና የግንባታ ቁጥጥር፣ የፕሮጀክት አስተዳደር እና ተዛማጅ መስኮች ላይ በከፍተኛ ጥራት የሰለጠኑ የባለሞያዎችን ቡድን የያዘ ነው።

Render of the Kefita Floor from outside

ኢትዮጵያ የሰው ዘር መነሻ ስትሆን የአህጉሩም ማዕከል ነች። ይህች ታላቅ የብዝኃነት ምድር፣ የታሪክ ሃብታም እና የበርካታ ዕድሎች ቋት የሆነች አገር እንግዳ አክባሪነትን ሰው ከመሆን ጸጋ ጋር ይዛ እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆን ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅምን የታደለች ነች። ከፍታ ደግሞ የኢትዮጵያን ትላንት፣ ዛሬ እና ነገን አጣምሮ ይዟል።

Kefita embodies Ethiopia’s past, present and future.

Play the Kefita video