ባለ ሁለት ወለል መኖሪያዎች
በዚህ የአዲስ አበባ አዲስና ልዩ መኖሪያ ውስጥ በውስጥ በወለሎቸ የሚለያዩ በደረጃዎች የሚገናኙት ዱፕሌክሶች ልዩ የኑሮ ዘይቤና ደስታ የሚፈጥሩ ናቸው። ዱፕሌክሶች የግልና የጋራ ቦታዎችን ለያይተው በሁለት ፎቆች የያዙ ናቸው። በአዲስ አበባ በአይነታቸው ልዩ ሆነው የቀረቡት እኚህ መኖሪያዎች ነዋሪዎች ቦታዎችን ለሚፈልጉት አይነት አገልግሎት መቀየር የሚያስችላቸውን ቦታ የያዙ ናቸው። ሰፋፊ የማብሰያና መመገቢያ ክፍሎች እንዲሁም ሰገነቶች ወዳጅ ዘመድ ሰብሰብ ብሎ ሊጫወትባቸው እጅግ ምቹ ናቸው። እኚህ ቤቶች በእርግጥም የሰማይ ሰገነቶች በመሆናቸው ጥቂቶች ብቻ ይህን የሚገርም ትዕይንት መኖሪያቸው ያደርጉታል።