February 19, 2021
የከፍታ አፓርትመንቶች የቅድመ ግንባታ የመጀመሪያው ሽያጭ ተጀምሯል። ትጉህ የሽያጭ ሰራተኞቻችን ጥያቄዎን ሊያስተናግዱ እና ለፍላጎትዎ የሚበጁትን አፓርትመንቶች ሊያስመርጡዎ ዝግጁ ናቸው።
ከፍታ አንድ መቶ ቅንጡ አፓርትመንቶች የሚኖሩት ሲሆን በባለ አንድ መኝታቤት፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት፣ ባለ ሶስት መኝታ ቤት፣ ዱፕሌክስ እና የህንጻው አናት ላይ በሚገኘው እጅግ ዘመናዊ በሆነው ፔንታውስ የተከፋፈሉ። የመኖሪያ ቤቶቹ አራተኛ ህንጻ ላይ ካለው የከፍታ ወለል የሚጀምሩ ሲሆን እያንዳንዱን መኖሪያ የከፍታ ሰገነት ላይ ያደርሱታል። ክፍት እና ዝግ ምግብ ማብሰያዎች፣ አገልግሎት መስጫዎች፣ በውስጣቸው ሰው የሚያራምዱ ቁምሳጥኖች /ልብስ ማስቀመጫዎች/፣ ከመኝታ ቤት ጋር ተያያዥ የሆኑ መታጠቢያ ቤቶችን በማካተት በተለያየ ገጽ የቀረቡት አማራጮች ዘመናዊና ሰፋ ያለ ቦታን ለሚጠይቅ የኑሮ ዘይቤ ተስማሚ ሆነው በነጠላ፣ በጥንድ፣ ከአነስተኛ ቤተሰብም ጋር ሆነ ለትላልቅ ቤተሰቦች ተስማሚ አማራጮችን የሚያቀርቡ ናቸው።
በረንዳና ሰገነቶቹ ሰፊ ሆነው ጥላ የሚያገኙ እንዲሁም አገልግሎት ላይ መዋል እንዲችሉ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው። ሰፋፊ ሰገነቶቹ ከመኖሪያ ክፍሎች /ሳሎን/ ጋር ተያያዥ ሆነው በግሩም እይታ ከቤት ውጪ ነፋሻ ጊዜን ለማሳለፍ ምቹ ናቸው።
ሶስት አሳንሰሮች ነዋሪዎችን በምቾት ከልዩው የከፍታ ወለል ጋር የሚያገናኙ ሆነው የሆቴል ድረጃን ከጠበቁት አገልግሎት መስጫዎች ጋር እንዲሁም ከመኪና ማቆሚያው ጋር የተገናኙም ናቸው። ሁለት የህንጻው ማዕከሎች ከከፍታ ወለል አንስተው እስከ ጣሪያው ድረስ ክፍት ሆነው የሚዘልቁ በመሆን ለህንጻው በቂ ብርሃንና ንጹህ የተፈጥሮ አየር ለማስገባት እንዲሁም በህንጻው ውስጣዊ ክፍል ቲያትር እና ድራማ ለማሳየት የሚሆኑ ናቸው።
ይህ ህይወት ያለው ህጻ ተፈጥሯዊ ይዘት ያለው፣ ውብ፣ በቀላል ወጪ የሚጠገን እና መሃል አዲስ አበባ ላይ በጥላ የተሞላ ፍጹም ሰላማዊ ጸጥታ ያለበት መኖሪያ ነው።