ባለ አራት መኝታ
እነዚህ ልዩ ባለ አራት መኝታ አፓርታማዎች ከፍተኛ ምቾት እና ነፃነትን እንዲሰጥ በሚያስችል የተለየ ዲዛይን የተሰሩ የመኖርያ ስፍራዎች ናቸው፡፡ ማራኪ የሆነው የወለል ንድፍ ስራቸው ለቤተሰብ በቂ እና ምቹ የሆነ እጅግ ሰፊና ውብ ክፍል፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር አስደሳች ጊዜ ለማሳለፍ ወይንም ስራን ከቤት ሆኖ በምቾት ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡ የመኖርያ ቤት ዲዛይኑ አስደሳችና ቁልፍ ገፅታ ሠፊ ሳሎኑን ከመመገቢያ ክፍሉ እና ቅርፁን እንደፈለጉት አድርጎ ለመጠቀም ከሚመቸው ማዕድ ቤት (ኪችን) ጋር ያጣመረ መሆኑ ነው፡፡
መኝታ ቤቱ ሰፊ ክፍል አና ዋና መታጠቢያ ክፍል ያካተተ ነው፡፡ ሌሎቹ መኝታ ክፍሎች የጋራ መፀዳጃ ቤት እና ልዩ የእንግዳ መታጠቢያ ክፍል አላቸው፡፡ አራተኛው መኝታ ቤት እንደ መስሪያ ክፍል ሊያገለግል ይችላል፡፡ እነዚህ አፓርታማዎች ለቤተሰብ ምቹና አስደሳች ህይወት በቂ ክፍሎችን ያሟሉ ናቸው፡፡




