ባለ ሁለት መኝታ
እኚህ መኖሪያ አፓርታማዎች እጅግ ማራኪ እና ምቹ ሲሆኑ፣ ግዙፍ መኝታ ቤት፣ ውብ ሳሎን፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ ለዐይን ክፍት የሆነ ውብ ማዕድ ቤት (ኪችን) እና ተጨማሪ ክፍል ያካተቱ ናቸው። ተጨማሪውን ክፍል ለሚፈልጉት ነገር ሊገለገሉበት ይችላሉ፡፡ ቢፈልጉ ተጨማሪ መኝታ ቤት ያደርጉታል፤ ካሻዎት ቢሮ ወይመ የእንግዳ ማረፊያ ወይም የልጆች ክፍል አድርገው ይጠቀሙታል፡፡
ሁሉም አፓርትመንቶች ወደ እንጦጦ ተራራ የሚያስቃኝ ግሩም እይታ አላቸው። ከአንዳንዶቹ መኖሪያዎች ጋር የሚቀርበው ሰገነት በተለያዩ ዝግጅቶች እንድግዶችን ለማስተናገድ ወይም እንደ ተጨማሪ የመዝናኛ ቦታ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። አፓርትመንቶቹ ለተወሰነ ጊዜ ለንግድ እንቅስቃሴ ለሚቆዩ ሰዎች፣ ለብቻቸው ለሚኖሩም ሆነ ለጥንዶች ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በኪራይ ለማቅረብ አዋጭ የኢንቨስትመንት ሃሳብም ናቸው።