ባለ ሶስት መኝታ
ለአገር ውስጥም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ውብ የመኖሪያ ስፍራ ነው። ባለ ሶስት መኝታ ቤት አፓርትመንቶች ሰፊ መኝታቤቶችን ዘና ከሚያደርግ እጅግ ሰፊ ዋና መኝታ ቤትን ከሰፊ ሳሎንና የምግብ ማበያ ጋር አዋህዶ ነዋሪዎች አስደሳች ምሽቶችን የሚያሳልፉባቸው ወይም ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ የሚያስተናግዱባቸው ናቸው። ያለው ቦታ በተፈለገ መልኩ ሊቀያየር የሚችል ከመሆኑም እንደ አማራጭ የሰራተኛ ክፍል፣ ክፍት ማብሰያ ክፍል እንዲሁም ተፈጥሮን ለሚያደንቁና ከቤት ውጪ ያሉ ቦታዎችን ለሚመርጡ ሰዎች ተስማሚ የሆኑ ሰገነቶችን ይዘዋል። ቅንጡና እንዳሻቸው የሚቀያይሩት ሰፊ ቦታ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች ወይም ጥንዶች በጣም ተስማሚ።



